“ሥራ አጥነትን መቀነስ ሰላምን ያመጣል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

33

ባሕር ዳር: ሰኔ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን እና የዋጋ ግሽበትን የውይይቱ ማዕከል ያደረገው የዛሬው የምክር ቤት ውሎ ሥራ አጥነት ቅነሳ፤ ምርት እና ምርታመነትን ማሳደግ የቀጣይ ጊዜ ትኩረት ይኾናል ተብሏል፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በሀገር ደረጃ የተቋቋመው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አበረታች ውጤቶች የታየበት ተቋም ኾኗል ብለዋል፡፡ ባለፈው በጀት ዓመትም ከ3 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ነው ያሉት፡፡

ግብርና፣ አገልግሎት፣ ኢንዱስትሪ እና የውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ዋና ዋና የሥራ እድል የተፈጠረባቸው መስኮች እንደነበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

ሀገራት ለሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ከ2 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገራት የሥራ እድል ፍላጎት እንዳቀረቡለት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቋሙን ካገዝነው ከዚህ የተሻለ አፈጻጸም ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በየዓመቱ ከ3 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎች ወደ ሥራ ገበያው ይሰማራሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ “ሥራ አጥነትን መቀነስ ሰላምን ያመጣል” ብለን እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ስጋቶችን አጥበን፣ እድሎችን አስፍተን፣ እንደ ሀገር ጸንተን መኖር ይገባናል ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የሕዳሴ ግድብ የራሷን በማያጓድል፣ የሌሎችን በማያሳጣ መልኩ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ፡፡