
ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያን የምርጫ ሥርዓት ለማጠናከር የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ሥርዓት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ፕሮጀክት በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ድርጅት መካካል ተፈርሟል፡፡
ፕሮጀክቱ ሶስት ግቦች ያሉት ሲሆን፦
➡አንድኛው የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን በማጠናከር ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ አሳታፊ፣ ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ሕዘበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር
➡ሁለተኛው ከሲቪክ ተቋማት ጋር በጋር በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ማሳደግ ሲሆን
➡ሶስተኛው ደግሞ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን መፍጠር መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ፕሮጀክቱ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት የሚተገበር ሲሆን የሀገሪቱን የምርጫ ሥርአት በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲን ለማስፈን አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ይጠቁማል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!