በመራዊ ከተማ አሥተዳደር ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እየተመረቁ ነው።

54

ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን መራዊ ከተማ አሥተዳደር 65 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እየተመረቁ ነው።

በከተማ አሥተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ መሰረተ ልማቶች ውስጥ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ፣ የጠጠር መንገድ፣ የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ስታዲየም፣ አዳዲስ የመብራት ትራንስፎርመሮች ተከላ፣ የመንገድ ዳር መብራቶች እና የጎርፍ ማፋሰሻ ቦዮች ይገኙበታል።

ከተጠናቀቁ መሰረተ ልማቶች ምርቃት ጎን ለጎን ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በከተማው ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ ይሰጣል። ለኢንቨስትመንት በተዘጋጀው 50 ሄክታር መሬት ላይ የመሰረት ድንጋይ እንደሚጣልም ተጠቁሟል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የቅዱሳን መኖሪያ፣ የዕውቀትና የጥበብ መፍለቂያ–ርእሰ አድባራት ወ ገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ”
Next articleየ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን ከሰኔ 26 እስከ 27/2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራው ተጠናቋል።