ሰራዊቱ የኢኮኖሚ አቅሞ ለሌላቸው ነዋሪዎች ቤት የመሥራት እና የመጠገን ድጋፍ አደረገ።

109

ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በቀጠናው የሚገኘው ሰራዊት በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ቦሌ ቀበሌ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤታቸውን በገንዘብ እና በጉልበት በመስራት ድጋፍ አድርገዋል ።

በዕለቱ የተገኙት ኮሎኔል ጌትነት ጅራ የክፍሉ ሰራዊት ለሕዝብ እና ለሀገሩ ሲል ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር የተቸገሩ ወገኖችን በተለያዬ ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እያደረገ መምጣቱን ገልጸው አሁንም በምንገኝበት አከባቢ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤታቸውን በመስራት እና በመጠገን ድጋፍ አድርገናል ብለዋል ።

የክፍሉ አባላት የክረምቱን ወቅት ተከትሎ በቆይታ ምክንያት ያረጁና ምቹ ያልሆኑ እንዲሁም ለማደስም ሆነ ለመስራት አቅም የሌላቸው ነዎሪዎች ቤት በመለየትና ድጋፍ በማድረግ አልኝታነቱን እያረጋገጠ መሆኑንም ገልፀዋል።

የቦሌ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ሱልጣን ሰይድ በበኩላቸው ሕዘባዊነት መለያው የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በከታማችንና በአከባቢያችን ለሚገኙ አቀመ ደካማ ነዋሪዎች ያደረገው ድጋፍ በእጅጉ የሚያኮራ ነው ብለዋል።

ሰራዊቱ ወደ አከባቢያችን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ድጋፍ እያደረገ ነው ያሉት አቶ ሱልጣን ሠራዊቱ በክረምቱ የመኖሪያ ቤታቸውን ማደስም ሆነ መስራት ላልቻሉ አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች ቤት የመሥራት እና የማደስ ድጋፍ በማድረጉ በነዎሪዎች ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

ድጋፉ የተደረገላቸው ነዎሪዎች በበኩላቸው የመኖሪያ ቤቶቻችን የፈራረሱብን እና የአንዳንዶቻችን ቤት ውኃ ሰለሚያፈስ ክረምቱ ሲገባ ጭንቀታችን ይበረታ ነበር እና እድሜ ለመከላከያ ሰራዊታችን ቤት ለሌለን ሰርተው እድሳት ለሚያስፈልን ጠግነው ከጭንቀት ገላግለውናል ምስጋናችን ወደር የለውም በማለት አሥተያየታቸውን ሰጥተዋል መረጃው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወቅቱ ከመቸውም ጊዜ በላይ መትጋትንና መብቃትን፣ ወደ እግዚአብሔርም መጮህን የሚጠይቅ ነው”ብፁዑ አቡነ አብርሃም
Next article“የቅዱሳን መኖሪያ፣ የዕውቀትና የጥበብ መፍለቂያ–ርእሰ አድባራት ወ ገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ”