የመቄት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ከ300 በላይ በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

58

ባሕር ዳር: ሰኔ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሌጁ ከደረጃ 1 እሰከ ደረጃ 4 በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 313 ተማሪዎች ዛሬ አሰመርቋል፡፡

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የመቄት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን አቶ ሞገስ መንጌ እንደገለጹት የማሰልጠኛ ኮሌጁ ክህሎትና እውቀታቸውን ያደበሩ ዜጎችን በማፍራት የድርሻውን እየተወጣ መኾኑን ገልጸዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብና በተግባር ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ሥራ ፈጣሪ በመኾን ሀገራቸውንና ወገናቸውን እንዲያገለግሉ አቶ መንጌ ሞገስ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተመራቂዎች በበኩላቸው በሰለጠኑበት ሙያ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጂ መኾናቸውን ተናግረዋል ።

መረጃውን ያደረሰን የመቄት ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየእስቴ – ስማዳ የኮንክሪት አስፋልት መንገድ እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ጊዜያዊ ርክክብ እንደሚደረግ የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ ኀላፊ ገለጹ።
Next articleየጂቡቲ መንግስት የሀገሪቱን የፖሊስ የክብር ኒሻን ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ሸለመ ።