
አዲስ አበባ: ሰኔ 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጋዜጠኛ ሕይወት ታደሰ ለልብ ህሙማን መርጃ ማእከል በማኅበራዊ ሚዲያ ያሰባሰበችዉን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚቆጠር ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጋለች።
የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሩይ አሊ ጋዜጠኛ ሕይወት ታደሰ በማኅበራዊ ሚዲያ ባሰባሰበችዉ ገቢ ከ50 ሚሊየን በላይ ገቢ ማድረጓ የሚያስደስት እና ለልብ ህሙማን ማእከሉ አስፈላጊ የኾነ የህክምና መሳሪያዎች ናቸዉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ማእከል እስከዛሬ ከ3000 በላይ ህጻናት እንዲታከሙ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዉ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ በመጠቀም የልብ ህሙማንን ማገዝ መለመድ አለበት ሲሉ ጠቅሰዋል።
ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ከ140 በላይ ቁሳቁስ ልደቷን አስመልክቶ መላኳን በመጥቀስ ሚዲያን ለመጥፎ አላማ ለሚጠቀሙ ሰዎች መማሪያ ይኾናልም ሲሉ ያነሱት ደግሞ የኢትዮጽያ የልብ ህሙማን መርጃ ማእከል የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ ናቸዉ።
ህክምና ማእከሉ ተጨማሪ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበትም በማለት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል።
በማእከሉ በአሁኑ ሰዓት ከ7000 በላይ ህጻናት ህክምና እየተጠባበቁ መሆኑም ተጠቅሷል።
ዘጋቢ:- ኤልሳ ጉኡሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!