የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች በደብረ ብርሃን ከባለሀብቶች ጋር እየተወያዩ ነው።

190

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ የአማራ ክልል ባለሀብቶች የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የክልልና የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሀብቶችና ሌሎች የማኅበተሰብ ክፍሎች እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ የተሳካላቸው ዘር ባለመምረጣቸው፣ በነበራቸው ርህርሄ በተለይም በጦርነት የማረኩትን ሳይቀር አክመው፣ ተንከባክበው ፍጹም ርህርሄ በማሳዬታቸው እንደነበር አመልክተዋል፤ ‹‹እኛም የአባቶቻችን ልጆች ነንና ወደ መጠፋፋት የፖለቲካ ሴራ እንገባም›› ብለዋል።

ታላቁ ንጉሥ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንድ ወቅት ለኢየሩሳሌም መነኮሳት በጻፉት ደብዳቤ ‹‹የሀገሬን ክብር ሳልመልስ አልተኛም›› ማለታቸውንም አስታውሰው ‹‹እኛም የሀገራችን ዕድገት ሳናረጋግጥ አንተኛም›› ብለዋል።

አዴፓ ከዘመኑ ጋር የሚዘምን፣ አንድ ቦታ ተቸንክሮ የሚቆም ፓርቲ አለመሆኑን ገልጸው ክልሉን ሁሉም መኖር የሚፈልግበት ምቹ ቦታ እንዲህን ሁሉም በጋራ እንዲሠራም ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ይርጉ ፋንታ -ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ

Previous articleደኢሕዴን አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባዔ ማካሄድ ጀመረ።
Next articleየባሕል ማዕከሉ ግንባታ ተጀመረ።