ቡና ባንክ የ11ኛ ዙር የውጭ ገንዘብ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ መርሐ ግብር አሸናፊዎችን ሸለመ፡፡

60

ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የቡና ባንክ አክሲዮን ማኀበር የውጭ ምንዛሬን ወደ ሕጋዊ መስመር በማስገባት ዜጎች በሕጋዊ መንገድ በባንክ እንዲመነዝሩ በማድረግ ሕገ ወጡን የጥቁር ገበያን ለመከላከል እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ባንኩ ደንበኞቹንም ለማበረታታት በማቀድ ያዘጋጀውን የ11ኛውን ዙር የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ አሸናፊዎችን ለይቷል።በብሔራዊ ሎተሪ አሥተዳደር አዳራሽ በተከናወነ የእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት አሸናፊ የእጣ ቁጥሮችንም በሕዝብ ፊት ይፋ አድርጓል።

በእጣ አወጣጡም 1ኛ እጣ የቤት አውቶሞቢል፣ ፍሪጆች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ዘመናዊ የውኃ ማጣሪያዎች እና ስማርት ስልኮች ናቸው፡፡

0007510 የኾነው የእጣ ቁጥርም የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ እጣ ሲኾን አሸናፊው ጌጤ አማረ ናቸው፡፡

0006820 አቶ አጋዤ መኮነን የፍሪጅ እጣ አሸናፊ ሲኾኑ 0000745የልብስ ማጣሪያ ማሽን እጣ አሸናፊ አቶ ታከለ ብርሃኑ ናቸው፡፡

የእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቡና ባንክ ማርኬቲንግና ኮሙኒኬሽን ዳሬክተር አቶ አባይነህ ሀብቴ አንድ ሀገር በኢኮኖሚ ልማት ዜጎቿን ተጠቃሚ ማድረግ የምትችለው ጤናማ የገንዘብ ልውውጥ ሥርዓት መዘርጋት ስትችል ነው ብለዋል። ቡና ባንክ የገንዘብ ዝውውሩ በኢኮኖሚው ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወት የበኩሉን አስተዋጾ እያደረገ መኾኑንም ተነግረዋል፡፡

ደንበኞቹም ሕጋዊ የኾነ የገንዘብ ዝውውርን በማከናወን ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ትብብራቸው እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፀደይ ባንክ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለን አምባሳደር አድርጎ ሾመ።
Next articleለአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኝ ማዘጋጀቱን የጎንደር ከተማ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።