
አዲስ አበባ፡ ግንቦት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ፀደይ ባንክ በ7 ነጥብ 75 ቢሊዮን ብር የተከፈለ እና በ11 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ካፒታል ወደ ባንክ ኢንዱስትሪ መግባቱ ይታወሳል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን ፤ ባንኩ በከፍተኛ በጀት ወደ ባንክ ኢንዱስትሪው መቀላቀሉን አንስተዉ፤ በማክሮ ፋይናንስ ዘርፉም ዝቅተኛ ማኀበረሰቡን ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።
ሰለሞን ቦጋለ በሀገራችን በሰብአዊነት የሚሠራቸዉ ሥራዎች የሚመሰገኑ መኾኑን አንስተዉ፤ ባንካችን አርቲስቱን አምባሳደር በማድረጉ ክብር ይሰማዋል ሲሉ አንስተዋል።
አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ በበኩሉ ባንኩ “የሁሉም ባንክ” የሚል ራዕይን ይዞ መነሳቱ የሚያስደስት ነዉም ሲል ተናግሯል።
ፀደይ ባንክ ማኅበራዊ ኀላፊነቱ እየተወጣም ይገኛል ብሏል።
ባንኩ በአሁኑ ወቅት 11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ካፒታል እና አጠቃላይ ሃብቱ 49 ነጥብ 7 ቢሊዮን መድረሱም ተገልጿል።
የደንደኞች ቁጥር ወደ 13 ሚሊዮን ሲኾን 600 የባንክ ቅርጫፎች እና 1ሺ የሚደርሱ ንዑስ ቅርንጫፎች እንዳሉትም ተጠቅሷል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!