
ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድህነትን ለማጥፋት ከሚሠራው ‘ገርልስ ኢፌክት’ ከተሰኘ መንግሥታዊ ያልኾነ ተቋም የኢትዮጵያ ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ውይይቱ ተቋሙ በኢትዮጵያ ሴቶችን ወደ ኋላ የሚጎትቱ ማኅበረሰባዊ እሳቤዎች ላይ ለውጥ ማምጣትና ታዳጊ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሚሠራበት ኹኔታ ላይ ያተኮረ መኾኑን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።
‘ገርልስ ኢፌክት’ እ.አ.አ 2008 የተመሰረተ ሲኾን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት የሚገኙ ታዳጊ ሴቶች(ከ10 እስከ 18 የእድሜ ክልል የሚገኙ) ከድህነት እንዲላቀቁ አላማ አድርጎ የሚሠራ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!