
ባሕር ዳር:ሚያዝያ 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአርበኞች የድል በዓል ቀደምት አባቶች በአንድነት በመቆም ድል ማድረግ እንደሚቻል ያረጋገጡበት ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
የዘንድሮው 82ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል “አብሮነት ለጽናትና ለድል” በሚል በአራት ኪሎ የድል ሐውልት በተለያዩ ሁነቶችእየተከበረ ይገኛል።
በወቅቱ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንደገለጹት፤ በብሔርና በሐይማኖት ሳይከፋፈሉ በአንድነት ስለቆሙ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ የመጣው ወራሪ ኃይል አንገት አስደፍተው መልሰዋል ብለዋል።
የወንድምና የእህቶች ደም በማፍሰስና በመጠላለፍ እድገትና ብልጽግና ሊመጣ አይችልም ብለዋል።
የጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ በበኩላቸው፣ ጀግኖች አባቶቻችን ባሳዩት ወደር የለሽ ተጋድሎ አንገታችንን ቀና አድርገን በኩራት አንድንራመድ አድርገውናል ብለዋል። በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጨምሮ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ማኅበር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!