
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አዋሽ ባንክ ለደንበኞቹ ህይወታቸውን መቀየር የሚያስችል ሽልማት መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
የአዋሽ ባንክ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ዮሃንስ መርጋ አዋሽ ባንክ የይቆጥቡ ይሸለሙ ፕሮግራም ሦስት ዓላማዎች እንዳሉት ገልጸዋል። የመጀመሪያው ቁጠባና የውጭ ምንዛሬን ማሳደግ ሲኾን ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠርና የአዋሽ ባንክ ደንበኞችን ማብዛት ዋና ዓላማ ያለው ስለመኾኑ አስገንዝበዋል።
የ10ኛው ዙር የአዋሽ ባንክ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር በአራት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲኾን፦
1.ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል መኪና
2.የባጃጅ ተሽከርካሪ
3.42 ኢንች ቴሌቪዥንና
4.ዘመናዊ የስልክ ቀፎ ያካተተ ነው።
የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል መኪና አሸናፊን ጨምሮ ሁሉም እድለኞች ሽልማታቸውን ከባንኩ ተቀብለዋል።
ዘጋቢ ፦ ባዘዘው መኮነን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!