“ግርማ ሕዝብን ለማገልገል ድንበር የማያውቅ መሪ ነበር” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

162

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአቶ ግርማ የሽጥላ አሰከሬን ሽኝት በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡ ክብራቸውን እና የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በሚመጥን መልኩ እየተካሄደ በሚገኘው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የግርማን ሞት መሥማት አብረናቸው ለሰራነው ለእኛ አሳዛኝም፤ አስደንጋጭም ነበር ያሉት ከንቲባዋ ግርማ የማይሞት ዓላማ ያነገቡ መሪ ናቸው ብለዋል፡፡ ግርማ ዕድለኛ ነው ላመነበት እውነት ሕይዎቱን አሳልፎ እስከመስጠትም ደርሷል ብለዋል፡፡

ሞት ሥጋን እንጂ ዓላማን አይገድልም ያሉት ከንቲባዋ ግርማ ማስመሰል አይችልም፣ ለእውነት ኖሯል ስለእውነትም አልፏል ነው ያሉት፡፡ “ግርማ ሕዝብን ለማገልገል ድንበር የማያውቅ መሪ ነበር” ያሉት ከንቲባዋ ግርማ የሕዝቦች ወንድማማችነት እና የኢትዮጵያ አንድነት የሚያስጨንቀው መሪ ነበርም ብለዋል፡፡ ግርማ ዘመኑን ሁሉ ቤተሰቡን ትቶ ሕዝብን ለማገልገል ሰርቷል ያሉት ከንቲባ አዳነች ቤተሰቦቹን መንከባከብ አሁን ባለው የግርማ የትግል ወንድሞች ትከሻ ላይ ያረፈ ነው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የፅንፈኛ ኃይሎቹን ትክክለኛ መልክና ገፅታ ለሕዝቡ በይፋ ያጋለጠ ነው” የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል
Next article“ማንኛውንም ሐሳብ ፊት ለፊት የሚሟገቱ፣ ፊት ለፊት የሚሟገቱትን እድል የሚሰጡ መሪ ነበሩ” ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር)