
ባሕር ዳር: ጥር 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባኤርቦክ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪ ኮሎናን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
በዚህም የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር በነበራቸው ውይይት የሀገራቱን ረጅም ዘመን የዘለቀ ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በመንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሚደረገው መልሶ ግንባታ ተግባራት ሁለቱ ሀገራት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሚኒስትሮቹ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የመልሶ ማቋቋምና የመደገፍ ስራዎች ሴቶችን ታሳቢ በማድረግ ላይ ያተኮሩ መሆን እንዳለባቸው በውይይታቸው ተነስቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!