ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚያስቃኝ ዐውደ ርዕይን ጎበኙ

252
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንጦጦ የሥነ-ጥበብ ማዕከል የተዘጋጀውን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የሚያስቃኝ ዐውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።
“ላሊበላ በእምነት የታነጸ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከጅማሬው አንሥቶ አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱን እና አሁን ያለበትን ሁኔታ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ ለዕይታ የበቁበት ነው።
በዐውደ-ርዕዩ የአብያተ ክርስቲያናቱ ታሪክ በቨርቹዋል ሪያሊቲ ወይም በቴክኖሎጂ የታገዘ ዕይታ ቀርቦበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን ትላንት አባቶች የሠሩትን ታሪክ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የሚያሳየውን ዐውደ ርዕይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንጦጦ ፖርክ በመምጣት እንዲጎበኝ ጥሪ አቅርበዋል።
ዐውደ ርዕዩ ለሁለት ወራት የሚቆይ ሲሆን ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። ዘገባው የኢቢሲ ነው።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር‼
Previous article“ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ!” ኢትዮጵያዊያን
Next articleቺርቤዋ ትክምቲ 15 ጌር 2015 ም.አሜታ