
ጥር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥትና ሕዝብ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃትና በድል መወጣት የሚያስችል ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ የምሥራቅ ዕዝ ኮር አመራሮች አረጋግጠዋል፡፡
በዕዙ የአንድ ኮር አመራር የኾኑት ሜጀር ጀነራል ሰለሞን ቦጋለ ጠላት ሚሌን ተቆጣጥሮ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንገት ለማስደፋትና ዋናውን የሀገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ መስመር ለመቁረጥ ያለ የሌለ ኃይሉን አሰልፎ የመጣውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ፍላጎት ቅዥት ኾኖ እንዲቀር አድርጓል ብለዋል፡፡
ሌላው አመራር ሜጀር ጀነራል ግዛው ኡማ በበኩላቸው የአሸባሪውን ቡድን አከርካሪ በመስበር ታሪክ የሚዘክረውና የተሰጠውን ተልዕኮ ኹሉ በላቀ ኢትዮጵያዊ ጀግንነት የተወጣው ዕዙ በቀጣይም በማንኛውም ጊዜ፣ ቦታና አካባቢ ተሰማርቶ የሚሰጠውን ግዳጅ በጀግንነት መፈፀም የሚያስችል ሞራል፣ ሥነ-ልቦናዊና ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡
በምሥራቅ ዕዝ የ2ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ እንደገለጹት ክፍለ ጦሩ የአሸባሪውን ቡድን ኮንክሪት ምሽጎችን በመደርመስና ጠላትን አንገት በማስደፋት ለእግረኛው ሠራዊት ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ በካሳጊታ ፣ በጭፍራና በዞብል ግንባሮች የተመዘገበው ድል ከፍተኛ መኾኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/