
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወረሪ ቡድን ከአማራ ክልል አካባቢዎች በወገን ጦር ድል ተደርጎ በወጣ ማግስት የሚከበሩት የልደት እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ከሌሎች የጸጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ቡድን ወርሯቸው ከነበሩ አካባቢዎች አንዱ በነበረው የላልይበላ ከተማ የሚከበረው የልደት በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ ከሌሎች የጸጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ጋር በቂ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ በጸጥታ ጥበቃ ሥራው የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ ተቋማት ተሳታፊዎች ናቸው ብለዋል፡፡
የልደት እና ጥምቀት በዓላት ያለምንም የሰላም እና የደኅንነት ስጋቶች እንዲከበሩ ግልጽ፣ ስውር፣ ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ጥበቃዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የፌደራል የጸጥታ ኃይሎች የእቅዱ ፈጻሚ ባለቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡
የሰላሙ ባለቤት የሆነው ሕዝቡ በተለይም ወጣቶች ጸጉረ ልውጦችን እና ሰርጎገቦችን በመከታተል እና የኬላ ፍተሻ በማድረግ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በትብብር እና በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡
በየአካባቢው የተጠናከረ የተቋማት ጥበቃ እና የ24 ሰዓታት የጸጥታ ፍተሻ ስለሚኖር ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና ቦታ ያለስጋት መንቀሳቀስ የሚችሉበት እድል ተፈጥሯልም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/