በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር በካናዳ ሊካሄድ ነው።

159
ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው የአማራና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር የፊታችን ቅዳሜ ታኅሣሥ 2/2014 ዓ.ም በካናዳ ቫንኩቨር ከተማ ይካሄዳል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በሚከናወነው የእራት ግብዣ ጨረታዎች፣ በበይነ መረብ የክፍያ አማራጮች ገንዘብ ማሰባሰብና ሌሎች መርኃ ግብሮች እንደሚካሄድ የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ (ኢክናስ) የብሪትሽ ኮሎምቢያ ቻፕተር ጸሐፊ አቶ ወብሸት ካሳ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
በመርኃ ግብሩ ላይ ከ200 እስከ 250 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በካናዳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ለተፈናቀሉ ወገኖች አሁን ከሚያደርጉት ድጋፍ ባለፈ በተጨማሪ ዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮ-ካናዳውያውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ የቶርንቶ ቻፕተር ባለፈው ቅዳሜ ሕዳር 25/2014 ዓ.ም በአማራና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ባካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ከ200 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ መሰብሰቡ የሚታወስ ነው፡፡
የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ (ኢክናስ) ከተቋቋመበት ሕዳር ወር 2013 ዓ.ም አንስቶ ከ278 ሚሊዮን ብር በላይ ለወቅታዊ ሀገራዊ ጥሪዎችና ለልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ማድረጉን አመልክቷል፡፡
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article“ጠላት ከሆነለት በየትኛውም ግንባር ይሁን ይጠብቀን” የአማራ ልዩ ኃይል አባላት
Next article“የሽብር ቡድኑ ግፍ በዋግ ሕዝብ ላይ”