
ሕዳር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ በጭፍራ ግንባር ተገኝተው ለሠራዊት አባላት ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም የሠራዊት አባላቱ ጀግኖች እንደሆኑ ገልፀውላቸዋል። “የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው” ብለዋል።
“የውስጥ ኃይሎች ለውጪ ወኪል ሆነው ኢትዮጵያን በሚወጉበት ወቅት በአንድነት ተነስተን አሸባሪዎችን ድባቅ እንመታለን” ነው ያሉት፡፡
ይህ ትውልድ በዚህ ታሪካዊ ወቅት አሸባሪውን #የመቅበር እድል በማግኘቱ ሊደሰት ይገባል ብለዋል።

ወደፊትም የአፋር ሕዝብ ሽብርተኛውን እስከ መጨረሻው #ለመቅበር ሁሉንም ነገር ያደርጋል ብለዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation