❝የሽብር ኃይሉን ግብዓተ መሬት ሳንፈጽም አንመለስም❞ የፋኖ አባላት

601
ሕዳር 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ፋኖ በሀገር ሕልውና ላይ የተቃጣን አደጋ ለመመከት ሲታገል ኖሯል፤ እየታገለም ይገኛል። የጭቆና አገዛዝን በመቃዎም ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለፍትሕ ተዋድቋል፤ እየተዋደቀም ይገኛል። ዛሬም አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኀይል በዋግኽምራ ግንባር እያርበደበደው ይገኛል።
በአካባቢው የፋኖ መሪ ከሆኑት መካከል ኮማንደር አረጋ አለባቸው እንዳሉት ፋኖ ሀገር በተደፈረች ጊዜ ቀድሞ የሚደርስ፣ አባቶች ያስከበሯትን ሀገር የሚያስቀጥል የሀገር አለኝታ ነው። በተለይም አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል የሀገሪቱን ሕልውና በተፈታተነ ጊዜ ተመሳሳይ ዓላማ ካነገቡ አደረጃጀቶች እና ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት በዋግ ምድር ጠላትን እየደመሰሰ ግስጋሴው ወደ ፊት መቀጠሉን ኮማንደር አረጋ ገልጸዋል።
በተለቀቁ አካባቢዎችም ሕዝቡን ወደ መደበኛ ሥራው እንዲመለስ እየተደረገ ይገኛልም ነው ያሉት።
❝ፋኖ የሽብር ኀይሉን ግብዓተ መሬት ሳይፈጽም አይመለስም❞ ብለዋል ኮማንደሩ።
ሌላው የፋኖ መሪ ሸጋው ማሞ በበኩላቸው ፋኖ በሀገሪቱ ላይ በውስጣዊ እና ውጫዊ ኀይሎች የተከፈተውን የተቀናጀ ጥቃት ለመመከት በግንባር እየተፋለመ ነው። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል የፋኖ ስም ሲነሳ ጉልበቱ እንደሚርድ የገለጹት ፋኖ ሸጋው የሽብር ኃይሉ በደረሰበት ምት ወደ ኋላ መሸሹን ገልጸዋል። አሁንም ፋኖ አሸባሪውን ኃይል እያሳደደው እንደሚገኝም ነው የነገሩን።
አሸባሪ ኀይሉ በቆፈረው ምሽግ ተቀብሮ እንደሚቀርም አንስተዋል። ማኅበረሰቡ ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ እያደረገ ያለው ተጋድሎ ወራሪውን ኃይል በአጭር ጊዜ ለመደምሰስ ለሚደረገው ትግል ትልቅ አቅም በመኾኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
ሌላው ምክትል አስር አለቃ ዋለልኝ አዝመራው ፋኖ በተለያዩ ግንባሮች በሽብር ኀይሉ ላይ አኩሪ ገድል እየፈጸመ ይገኛል ብለዋል።
አሁንም በዋግኽምራ ግንባር ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት በተካሄደ ፍልሚያ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን ነው ያነሱት። ያሰለጠናቸው የመረጃ ሰዎች ጭምር መያዛቸውን ነግረውናል።
የሽብር ኀይሉ በተደጋጋሚ ያደረገው የጥቃት ሙከራ በጀግኖች ተመትቶ ተመልሷል ብለዋል።
ያለ ትግል ሕልውናን ማረጋገጥ እንደማይቻል የገለጹት የፋኖ አባሉ ወጣቶች ሁለገብ ትግል በማድረግ ይህንን አሸባሪ ኀይል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስጋት እንዳይኾን ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግንባር አመራር እየሰጡ እንደሚገኙ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡
Next articleከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን በመሰለፍ ጠላትን በቁጣ አለንጋቸው እየገረፉ እንደሚገኙ የአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ አባላት ገለጹ።