
ሕዳር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ)አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ለመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጠራው “#NOMORE“ዘመቻ ሰልፍ በካናዳ ኦቶዋ ተካሂዷል፡፡
በሰልፉ ላይ በካናዳ ኦቶዋ፣ ቶሮንቶ፣ ሞንትሪያል፣ ኩቤክ፣ ስካርብሮ፣ ኪንግስተን እና ሌሎች ከተሞች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትና የኤርትራ ዜጎች ተሳትፈዋል፡፡
አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚያወግዙ፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ እየሠሩ ያሉትን ግጭት አባባሽ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዲያቆሙ ጥሪ የሚያደርጉ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ ተላልፈዋል፡፡

ለካናዳ ፓርላማ እና በኦቶዋ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙና እጃቸውን እንዲያነሱ የሚያስገነዝብ ደብዳቤ እንደሚሰጥም ተገልጿል።
የተካሄደው ሰልፍ አንዳንድ የምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና በመቃወም በመላው ዓለም በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የሚከናወነው ሰልፍ አካል መሆኑን ከዲያስፖራ ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ