
ባሕር ዳር: ሕዳር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በቀጣናው የኢትዮጵያን መሪነት ለማረጋገጥ፤ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የአሜሪካ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በመከባበርና በጋራ ተጠቃሚነት መንፈስ ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል አመለከተ።
የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ እየተከተለ ያለውን የተሳሳተ አካሄድ በማውገዝ ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መግለጫ ልኳል።
በመግለጫውም በቅርቡ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይና የመከላከያ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የተሰጠውን የጣልቃ ገብነት ሃሳብ ተቃውሟል።
አሜሪካ የጦር ኃይሏን በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ለማሳተፍ የተነሳውን ሃሳብ ስህተትነት ያስገነዘበ ሲሆን “መላው የአሜሪካ ሕዝብም ከአፍጋኒስታን የጆ ባይደን ፖሊሲ ውድቀት በኋላ ይህ በአፍሪካ እንዲደገም አይፈቅድም”ብሏል።
መግለጫው አክሎም በኢትዮጵያ የተከሰተው ግጭት የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ አስተዳደሩ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ እንድትፈታ ሊተዋትና የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር የሚያባብሱ ተግባራትን ከማከናወን ሊታቀብ እንደሚገባው አሳስቧል፡፡
የአስተዳደሩ የተሳሳተ ፖሊሲና ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን የማራመድ ሃሳብም በአሜሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጿል።
አሜሪካ ኢትዮጵያን በተመለከተ በመከተል ላይ ያለችውን የተሳሳተ ፖሊሲ ዳግም ማጤን እንዳለባት አሳስቧል፡፡ ለ118 ዓመታት የቆየውን የኢትዮ-አሜሪካ ወዳጅነት ለማጠናከርና ኢትዮጵያ የቀጣናው ሰላምና መረጋጋት መሪ እንድትሆን ለማስቻል አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ ጋር በመከባበርና በጋራ ተጠቃሚነት መንፈስ ሊሠራ እንደሚገባው ማስገንዘቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወራሪውን ጠላት ደምስስ!
የጀግንነት ታሪክህን ዳግም አድስ!
ነፃነትህን አትስጥ!
ተዋርዶ ከመኖር በክብር መሞት ይሻላል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ