
ለባሕር ዳርና አካባቢው የግልና የመንግሥት ታጣቂዎች፣ ለተጠባባቂ ኀይሎች እንዲሁም በአዲስ ወደ ልዩ ኀይል መቀላቀል ለምትፈልጉ በሙሉ!
ወራሪው፣ አሸባሪውና ተስፋፊው የትህነግ የጥፋት ቡድን በክልላችን በተለይ ደግሞ በሰሜን ወሎ፣ በዋግኽምራ፣ በደቡብ ወሎና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በመውረር በያዛቸው አካባቢዎች የአማራን ሕዝብ አንገት በሚያስደፋ መልኩ ንፁሃንን ጭምር በመድፈርና በመግደል እንዲሁም ከቤት የአገኘው ሲያልቅበት አርሶ አደሩ አንድ ዓመት የለፋበትን አዝመራ በማጨድ ወደ ትግራይ እያጓጓዘ ይገኛል።
የክልላችን መንግሥት የዚህን ወራሪ ኀይል እድሜ በማሳጠር አደጋ ውስጥ ያለውን ሕዝባችን ለመታደግ ቀደም ብሎ የክተት አዋጅ በሁሉም ዘርፍ ወደ ግንባር እንዲሆን ጥሪ አስተላልፏል።
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር የክልላችን ጥሪ ተከትሎ በሁሉም ዘርፎች አዲስ ንቅናቄ የጀመርን መሆኑ ይታወቃል።
ይህን ወራሪ ኀይል ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ልዩ ኀይላችን፣ ፋኖና ሕዝባዊ ሚሊሻዎች ከጀግናው አየር ኀይላችን ጋር በመሆን በገባበት ሁሉ በሰላም እንዳይመለስ አስፈላጊውን እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም ከቡድኑ አረመኔነትና አውዳሚነት አንፃር በቀላሉ ለመቆጣጠር የሁሉም ተሳትፎ አስፈላጊ ሁኗል።
ስለሆነም ሀገራችንና ክልላችን ከዚህ ወራሪና አሸባሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ከዚህ በታች በአለው አደረጃጀት እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
1/ለአማራ ልዩ ሃይል፦
እድሜያችሁ ከ18 እስከ 25 የሆነ የትምህርት ዝግጅት ከ4ኛ ክፍል በላይ የሆናችሁ፣
የመመዝገቢያ ቦታ፦ በሁሉም ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያዎች ሲሆን የመመዝገቢያ ጊዜ ከጥቅምት 15 እስከ 21/2014ዓ.ም
2/ካሁን ቀደም በመጀመሪያና በሁለተኛ ዙር የተጠባባቂ ኀይል ስልጠና የወሰዳችሁ በየትኛውም ግንባር ተሰልፋችሁ ለማገዝ ዝግጁ የሆናችሁ በሙሉ፦
በተመሳሳይ በክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያዎችና ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት እየተገኛችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናስተላልፋለን።
3/በከተማችን ለምትኖሩ ማንኛውም የግልና የመንግስት ታጣቂዎች በሙሉ፦
በየአካባቢያችሁ ፖሊስ ጣቢያና ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት በመመዝገብ ለአካባቢ ሰላምና በየትኛውም ግንባሮች ድረስ ካሉ የፀጥታ አካል ጋር ተቀናጅተን ጠላትን ድል ለማድረግ ዝግጁ የሆናችሁ ሀሉ እየመጣችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር
ጥቅም 15/2014ዓ.ም
ባሕርዳር