
ደሴ: መስከረም 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን አሸባሪው የትህነግ ቡድን በወረራቸው የተለያዩ አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ባለመኖሩና የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ በርካቶች በስቃይ ውስጥ መሆናቸውን ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ወገኖች ገልጸዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በአቅመ ደካሞች፣ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ በፈፀመው አሰቃቂ ግፍ ለሞት መዳረጋቸውንና በሕይወት የተረፉትም በርሃብ እና በመድኃኒት እጥረት ምክንያት በችግር ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች በአካባቢዎቹ በመግባት የሰብዓዊ ድጋፎችን እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል፡፡



ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ