
ሰቆጣ፡ ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሰሃላ ሰይምትን እና ዝቋላን በሚያካልለው የተከዜ ወንዝ ኮሪደር ተገን አድርጎ አካባቢውን ሲዘርፍ የነበረው የአሸባሪው ትህነግ ቡድን አባላት በአካባቢው ሚሊሻ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡
የአሸባሪው ትህነግ ቡድን አባላት ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ በስሃላ ሰየምት እና ዝቋላ አካባቢ የዘረፉትን ሃብት እና ንብረት ወደትግራይ ለማሸሽ ጥረት ላይ እያሉ በድንበር አካባቢዎች መሽጎ የነበረው የአካባቢው የሚሊሻ አባላት እና ወጣቶች ሙሉ በሙሉ ደምስሰውታል፡፡
ከስሃላ ሰየምት ተባሮ ወደ ዝቋላ የገባውን የአሸባሪ ቡድን በመደምሰስ የምዕራብ እና የምስራቅ በለሳ ሚሊሻዎች ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡
የሰሃላ ሰየምት እና ዝቋላ ወረዳዎችም ከአሸባሪ ቡድኑ በማስለቀቅ በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ቁጥጥር ስር ገብተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ከፍያለው ደባሽ -ከስሃላ ሰየምት
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m