ጁንታውን ለመደምሰስ በሚደረገው የህልውና ዘመቻ የእነቴጌ ጣይቱን ታሪክ ለመድገም ቆርጠን ተነስተናል” በምዕራብ ጎጃም ዞን ለህልውና ዘመቻ ስንቅ የሚያዘጋጁ ሴት አርበኞች

205

ጁንታውን ለመደምሰስ በሚደረገው የህልውና ዘመቻ የእነቴጌ ጣይቱን ታሪክ ለመድገም ቆርጠን ተነስተናል” በምዕራብ ጎጃም ዞን ለህልውና ዘመቻ ስንቅ የሚያዘጋጁ ሴት አርበኞች

ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠላቴ ብሎ የፈረጀውን አማራን ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳው የትህነግን ርዝራዥ ቡድን ለመደምሰስ በግንባር ከሚደረገው የጸጥታ ኀይሉ ጦርነት ባሻገር ሕዝቡ በተደራጀ መንገድ ገንዘብ እና በአይነት በማሰባሰብ አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የሚገኙ ሴቶችም በአደረጃጀታቸው ጁንታውን እየተፋለመ ለሚገኘው የጸጥታ ኀይሉ የሚኾን ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡ “የእነቴጌ ጣይቱን ታሪክ የምንደግምበት ጊዜው አሁን ነው” ያሉት በደቡብ አቸፈር ወረዳ ዱርቤቴ ከተማ ግንባር ለሚፋለመው የጸጥታ ኀይል ስንቅ ሲያዘጋጁ ያገኘነቸው ሴት አርበኞች ናቸው፡፡May be an image of 2 people, people sitting and outdoors

በስንቅ ዝግጅቱ ላይ ያነጋገርናቸው ወይዘሮ ፋሲካ እንዳለው እና ወርቅነሽ ጉዳይ ከስንቅ ዝግጅቱ ባሻገር እስከ ህይዎት መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ በህልውና ዘመቻው የሴቶች ተሳትፎ በጦርነቱ ግንባር ከመሰለፍ ባሻገር ስንቅ በማዘጋጀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደኾነ የገለጹት የደቡብ አቸፈር ወረዳ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ወይዘሮ ጎጃም ዓለም ናቸው::

ትህነግ ለሴቶችና ህጻናት የማይራራ አረመኔና አሸባሪ ቡድን ነው ያሉት ወይዘሮ ጎጃም ”ለህልውናችን ስንል ጦርነቱን በድል ለማጠናቀቅ ሴቶች የድርሻችንን እንወጣለን” ብለዋል::

እንደ ሀገር የገጠመንን ፈተና ለመወጣት የዞኑ ማኅበረሰብ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ጎን በመቆም ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት ደግሞ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ስሜነህ አያሌው ናቸው።May be an image of 5 people, people standing, people sitting and outdoors

ዞኑ የሚሊሻ አባላትን ወደ ግንባር የላከ ሲኾን ለጸጥታ ኀይሉ በሁለት ዙር በጥሬ ገንዘብ እና በአይነት ሀብት በማሰባሰብ የላከ መኾኑን አስታውቀዋል:: እንደ ዞን 456 ሚሊዮን በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ሀብት ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን ከ 34 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በጥሬ ገንዘብ ሀብት ተሰብስቦ ገቢ መደረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ እቅዱን ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው አሁን ላይ በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች በሴቶችና በወጣቶች አደረጃጀት የተዘጋጀ በአይነት ደረቅ ሬሽ ተሰብስቦ ወደ ግንባር ለሁለተኛ ዙር መላኩን ተናግረዋል::

አሁን ላይ ከ200 ኩንታል በላይ ደረቅ ሬሽን፣ 2ሺህ ሊትር በላይ ዉኃ እና በአይነት በየወረዳው ተዘጋጅቶ ወደ ግንባር በመጓጓዝ ላይ ነውም ብለዋል:: የሀብት ማሰባሠቡ ይቀጥላል ያሉት አቶ ስሜነህ ሕዝቡ ሰርጎ ገቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡No photo description available.

ዘጋቢ፦ ዘመኑ ይርጋ – ከፍኖተ ሰላም

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“በሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳ የሚያዝም ሆነ የሚለቀቅ ቦታ የለም” የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ
Next articleሰዓተ ዜና ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ)