በህልውና ዘመቻ ለተሰማራው ሠራዊት በኦሮምያ ክልል የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች የስንቅ ድጋፍ አደረጉ፡፡

106
በህልውና ዘመቻ ለተሰማራው ሠራዊት በኦሮምያ ክልል የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች የስንቅ ድጋፍ አደረጉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮምያ ክልል በሚገኙ 6 ዞኖች እና 12 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ በህልውና ዘመቻ ለተሰማራው ሠራዊት አገልግሎት የሚውል ስንቅ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ድጋፉን ለማስረከብ ከኦሮምያ ክልል ልዑኩን መርተው የመጡት አቶ እንዳሻው ብርሃኑ እንደተናገሩት አሽባሪውን ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው ትግል ተሳታፊ ለኾኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ስንቅ የሚሆን 650 ሰንጋዎችን እና 680 በግ እና ፍየሎችን ማስረከባቸውን ተናግረዋል።
ድጋፉን ይዞ የተገኘው ልዑክ ጎንደር ከተማ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሕዝቡ ተወካይ የኾኑ አባ ገዳዎች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በሰጡት አስተያየትም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ነገም አንድ ነን ብለዋል፡፡
አንድነትን ለማፈራረስ የሚመጣን ጠላት ለመዋጋት በአንድነት መቆም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሕዝቡ አንድነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ገለጹት፡፡
በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሞላ መልካሙን ጨምሮ የጎንደር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል፡፡
የስንቅ ድጋፉን የተረከቡት በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምዕራብ እዝ 33ተኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ እና ሎጀስቲክስ ኀላፊ ኮሎኔል ደጀኔ ደበሬ እንደተናገሩት አሽባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተሰጠውን ኀላፊነት እየተወጣ ነው፡፡ የኦሮምያ ክልል ላደረገው የአጋርነት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡ ሕዝቡም ከመከላከያ ጎን ለመቆም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኃይሉ ማሞ-ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleʺከእንግዲህ አይኖርም ነገር ማለሳለስ ፣ እነርሱም አያርፉም እኛም አንመለስ “
Next articleየሲዳማ ክልል ሁለተኛ ዙር የልዩ ኃይል አባላትን ለሀገራዊ ጥሪ ሊልክ ተዘጋጅቷል፡፡