
ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር ከተለያዩ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት ማሳለፍ እንደሚገባ የደቡብ ወሎ ዞን እስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ ከድር ሁሴን ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሽህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በኮምቦልቻ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን እስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ ከድር ሁሴን ሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር ከተለያዩ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በመርዳትና ከጎናቸው በመሆን ማሳለፍ ይገባናል ብለዋል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ምክትል ተቀዳሚ ከንቲባ ኢንጂነር አሕመድ የሱፍ እንደተናገሩት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሲያከብሩ በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት የሚደረገውን የህልውና ዘመቻ በሁለንተናዊ መልኩ መደገፍ ይገባዋል፤ የአሸባሪው ትህነግ ርዝራዦች በኅብረተሰቡ ውስጥ ተሰግስገው ለጥፋት ድግስ ተዘጋጅተዋልና እነዚህን የአማራ ሕዝብ ጠላቶች ነቅተን መጠበቅና ሊያደርሱ የሚችለውን ጥፋት መከላከል ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡

ሕዝበ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሲያከብር የሃገሩንና የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ በመጠበቅ እና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት መሆን እንዳለበት በበዓሉ አከባበር ወቅት ተገልጿል፡፡
በየአካባቢው የሚገኙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት በዓሉን ተደስተው እንዲያሳልፉ ማድረግ ይገባልም ተብሏል፡፡
የሃይማኖቱ ተከታዮች የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሊት በስኬት በመከናወኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ሕዝብ ጠላት የሆነው የአሸባሪው ትህነግ ቡድንን በመመከት በኩልም ሕዝበ ሙስሊሙ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ እና መስዋእትነት ለመክፈል ጭምር ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
ዘጋቢ፡- አሊ ይመር – ኮምቦልቻ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
