የጎንደር ከተማ ሴቶች ለዘመቻ ህልውና የኋላ ደጀን ለመሆን የስንቅ ዝግጂት እያደረጉ ነው።

152
የጎንደር ከተማ ሴቶች ለዘመቻ ህልውና የኋላ ደጀን ለመሆን የስንቅ ዝግጂት እያደረጉ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው የትህነግ ቡድንን የጥፋት ተልዕኮ ለመከላከል ግንባር ለሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል እና ሚሊሻ አባላት የጎንደር ከተማ ሴቶች የስንቅ ዝግጂት እያደረጉ ነው።
በሕግ ማስከበር ዘመቻው ወቅትም የስንቅ ዝግጂት ማድረጋቸውን የተናገሩት የጎንደር ከተማ ሴቶች አሸባሪ ቡድን ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰስ ድረስ ድጋፋችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የአማራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጠላት የሆነውን አሸባሪ ቡድን በግንባር ለሚከላከለው የጸጥታ ኀይል የኋላ ደጀን በመሆን ሴቶች በትግል ወቅት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንደሚወጡም ተናግረዋል።
አሸባሪው ቡድን በኢትዮጵያውያን ላይ የደቀነውን ስጋት ለመቀልበስ ግንባር ድረስ በመሄድ ለመታገልም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ወደ ግንባር የዘመቱ የሚሊሻ ቤተሰቦችን በሚችሉት ሁሉ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውንም ለአሚኮ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:– ዳንኤል ወርቄ– ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“አሸባሪው ህወሓት በሚፈጥረው ግጭት ምክንያት ችግር ውስጥ የሚገባው ከአማራ ክልል ጋር ብቻ ሳይሆን ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሆነ የኦሮሚያ ወጣት ማኅበር ፕሬዚዳንት ወጣት ከድር እንዳልካቸው አስታወቀ።
Next articleየቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ዛሬም እንደ ትናንቱ አሸባሪውን ቡድን ለመፋለም ተዘጋጅተዋል።