ኅብረቱ በብሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ፡፡

224

የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ የብሩንዲ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ፡፡

በሶማሊያ ለሰላም ማስከበር ሥራ የተሰማሩ የብሩንዲ ወታደሮች ጥቃት እንደደረሰባቸው ኅብረቱ አስታውቋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ቅዳሜ በሶማሊያ ሰሜናዊ ክፍል ሂርሻበሌ በተባለው አካባቢ ልዩ ተልዕኮ በመወጣት ላይ እያሉ ነው፡፡  የአልሸባብ የሽምቅ ተዋጊዎች እንደፈጸሙትም ወታደራዊ መረጃዎች ያሳያሉ ተብሏል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ ህይዎታቸው ያለፈ ወታደሮች ስለመኖራቸው እንጂ የጉዳቱን መጠን አላመላከተም፡፡

ኅብረቱ በሰላም አስከባሪ ወታደሮች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በፅኑ እንደሚያወግዘው አሳውቋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት የተሰውት የብሩንዲ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የኅብረቱን ልዩ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በፅናት ሲወጡ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ ለተጎጅ ቤተሰቦችና ለብሩንዲ መንግስትም የሀዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቀሪ የኅብረቱ አባል ሀገራት በሶማሊያ የተረጋጋ ሰላምና ጸጥታ እንዲኖር መስራት እንደሚኖርባቸውም ሙሳ ፋቂ ማህማት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ብሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ ወታደሮቻቸውን በአሚሶም ልዩ ተልኮ እያሳተፉ የሚገኙ ሀገሮች ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

በሀይሉ ማሞ

Previous articleኅብረቱ በብሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ፡፡
Next articleቺርቤዋ 30 12 2011