በኢትዮጵያ ከ60 ዓመታት በላይ ሲያገለግል የቆየው የንግድ ሕግ ተሻሻለ፡፡

238
በኢትዮጵያ ከ60 ዓመታት በላይ ሲያገለግል የቆየው የንግድ ሕግ ተሻሻለ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 16/2013 (አብመድ) በኢትዮጵያ ላለፉት 62 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የንግድ ሕግ ማሻሻያ ተደረገበት።
የንግድ ሕጉን ማሻሻያ ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል።
በምክር ቤቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ መሰረት አባተ የንግድ ሕጉን ረቂቅ አዋጅ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ባለፉት 34 ዓመታት የንግድ ሕጉን ለማሻሻል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም ማሻሻያው ለምክር ቤቱ የቀረበው በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውሰዋል።
ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ አዋጁን የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በዝርዝር አይቶ ማሻሻያ ማድረጉንም ነው የገለጹት።
ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት የንግድ እንቅስቃሴ አኳያ ለነጋዴው የተሳለጠ አሠራር መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ሰብሳቢዋ በተለይ ሀገሪቷ የዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ያሳልጣል ብለዋል።
የምክር ቤቱ አባላትም የሕጉ መሻሻል በተለይ በንግዱ ዘርፍ የሚታዩ ህገወጥ አሠራሮችን ለማሻሻልና ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ መሆኑን እንደገለጹ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ምርጫ በሂደቱ እንጂ በውጤቱ አይለካም” የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር
Next articleየአማራ ልዩ ኃይልን በተሳሳተ መንገድ መተቸቱና መኮነኑ መሰረተ ቢስና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ፡፡