መላው የአማራ ሕዝብ አንድነቱን እንዲጠብቅ አቶ ዮሐንስ ቧያለው አሳሰቡ፡፡

150
መላው የአማራ ሕዝብ አንድነቱን እንዲጠብቅ አቶ ዮሐንስ ቧያለው አሳሰቡ፡፡
ባሕር ዳር፡ የካቲት 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሐራ ከተማ አስተዳደርነት ዕውቅና፣ ምስጋናና የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ቧያለው አሳስበዋል፡፡
ሐራ ዛሬ ትንሽ ከተማ ብትሆንም ቢያንሰ ሶስት ክልሎችን ታገናኛለች፡፡ ወደፊት ደግሞ ጅቡቲን፣ አስብንና ምፅዋን የምታገናኝ ናት ነው ያሉት አቶ ዮሐንስ፡፡ ሐራ ወደፊት የባቡር ጣብያ ብቻ ሳትሆን የባቡር መገናኛዎች ቁልፍ ከተማ እንደምትሆን ማሰብ መቻል አለብን ብለዋል፡፡
እሳቤያችን አሳንሰን ካየነው ከተማ መገንባት ሳይሆን ማበላሸት ነው ያሉት አቶ ዮሐንስ ከተማዋን ለሥራ ምቹ ማድረግ ይጠበቃልም ብለዋል፡፡ እሳቤዎች ሁሌም ከፍ ማለት አለባቸውም ነው ያሉት፡፡
ከተማዋ በመሠረተ ልማት የተመቻቸች እንድትሆን መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ከተማዋን የፍቅር ከተማ አድርጎ በማስቀጠል ሠላም የሰፈነባትና የመቻቻልና የአብሮነት እሴቷን ጠብቃ መሄድ አለባትም ብለዋል፡፡ አንድነታችሁን ጠብቃችሁ መሄድ አለባችሁ ሲሉ ለታዳሚዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በአካባቢው ያለው መቻቻልና አንድነት ወደሌላው አካባቢ እንዲሰፋ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ መላው የአማራ ሕዝብ አንድነቱን ጠብቆ እዲሄድም አቶ ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡
በአንድ አካባቢ የሚለማ ልማት የአማራ ልማት እንደሆነ ሁሉ በአንድ አካባቢ የሚጠፋ ጥፋትም የአማራ ጥፋት መሆኑን አውቀን ጠንካራ አንድነት መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ልማት ሲሆን በጋራ እናለማን ጥቃት ሲመጣም በጋራ መከላከልና በጋራ መትመም ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡ ወጣቶች ለመጪው ምርጫ የሰላም ጠበቃ መሆን አለባቸውም ብለዋል፡፡ ወጣቶች ከስሜት የፀዳ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድና ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ለአካባቢ ፣ ለሀገርና ለወገን ሠላም መሆን እንዲተጉም አደራ ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleከተሞችን የእድገት ማዕከል ለማድረግ ለ54 ከተሞች ሽግግር መፈቀዱን የአማራ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ ገለጸ።
Next articleየኢትዮጵያና አሜሪካ ወዳጅነት እንዲጠናከር ተግተው እንደሚሠሩ አዲሷ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ገለጹ፡፡