ጥምቀት በወልድያ

259
ጥምቀት በወልድያ
ባሕር ዳር፡ ጥር 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) በወልድያ የጥምቀት በዓል ሥነ ስርዓት እየተከናወነ ነው። ትላንት ጥር 10 ለዛሬ ጥር 11 አጥቢያ ሌሊት የስርዓተ ማህሌት፣ ኪዳንና የቅዳሴ ስርዓት ተከናውኗል። ሲነጋም ለጥምቀት ስርዓቱ በተዘጋጀው ጸበል ዙሪያ ካህናትና ምዕመናን ከበው ስርዓተ ቅዳሴ ተደርሷል።
ቀጥሎም የተዘጋጀው ጸበል በብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎና በአማራ የኦሮሞ ብሔረሰብ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የቅዱስ ላል ይበላ አቢያተ ክርስቲያናት የበላይ ጠባቂ ተባርኮ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። የስርዓተ ጥምቀቱ መታሰቢያ የጸበል ርጭትም እየተከናወነ ነው።
በዋሴ ባየ እና በባለ ዓለምዬ – ከወልድያ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleጥምቀት በከሚሴ
Next articleጥምቀት በደባርቅ ከተማ