
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብን ለማጠናከር ያለመ የንግድ ትርኢት እና ባዛር በጎንደር ተከፍቷል፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) ክለቡ እራሱን በገንዘብ ለማጠናከር ከከፈተው የንግድ ትርኢት እና ባዛር በተጨማሪ በሚያካሂደው የሩጫ ውድድር ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ እየሠራ ነው፡፡

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ያለበትን የገንዘብ ችግር በመፍታት በኩል ትልቅ ሚና እንዳለውም የንግድ ትርኢት እና ባዛሩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ የሚፈልጉትን እቃ በርካሽ ከመግዛት ባለፈ ከክለቡ ጎን መቆማቸውን ለማሳየት እንዳገዛቸውም ጠቅሰዋል፡፡
የፋሲል ከነማ የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ኀይለማርያም ፈረደ ክለቡን በገንዘብ ለማጠናከር ታስቦ የንግድ ትርኢት እና ባዛሩ መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ በቀጣም የሩጫ ውድድሮች እና ሌሎች ዝግጅቶችን በማካሄድ ገቢ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
በሚካሄደው የንግድ ትርኢት እና ባዛር 2 ሚሊዮን ከሩጫ ውድድሩ ደግሞ 3 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት በእቅድ ተይዞ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

ደጋፊዎች ክለቡን ሜዳ ውስጥ ተገኝቶ ከመደገፍ ባለፈ በገቢ ማስገኛ ዘዴዎች በመሳተፍ አስፈላጊውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በንግድ ትርኢት እና ባዛሩ ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ተሳታፊ መሆናቸውንም አብመድ በቦታው ተመልክቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ምስጋናው ብርሃኔ-ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ