
ፋና የህጻናት እና ማኅበረሰብ ልማት ማኅበር የልደት በዓልን ከአረጋዊያን ጋር አሳልፈዋል።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 29/2013 ዓ.ም (አብመድ) ከተመሰረተ 14 ዓመታትን ያስቆጠረው ፋና የህጻናት እና ማኅበረሰብ ልማት ማኅበር የልደት በዓልን ረዳት ከሌላቸው አረጋዊያን ጋር አሳልፏል።
ማኅበሩ በአረጋዊያን ማዕከሉ የምሳ ግብዣ በማድረግ አረጋዊያንን አግድፏል። የማኅበሩ አባላትና እና የባሕር ዳር ከተማ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ማኅበሩ በዓመት ሦስት በዓላትን ከአረጋዊያን ጋር ያሳልፋል ያሉት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ አቶ ተፈራ አባተ ይህ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል እንሠራለን ብለዋል።
መረዳዳት የኢትዮጵያዊያን ነባር ባሕል ነው ያሉት የባሕር ዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ባየ አለባቸው “ወደነበርንበት ማኅበራዊ እሴት እና ከፍታ መመለስ አለብን” ብለዋል። በዚህ የበጎ አድራጎት ተግባር ለተሳተፉ ወጣቶች፣ ባለሃብቶች እና ተቋማት ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ከንቲባው ከተማ አስተዳደሩ ከጎናቸው መሆኑንም አረጋግጠውላቸዋል።
የተደረገላቸው ድጋፍ እንዳስደሰታቸውም ያነጋገርናቸው አረጋዊያን ተናግረዋል። ማህበሩ ለ149 አረጋዊያን የምሳ ግብዣ እና የቅርጫ ስጋ አከፋፍሏል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ