
የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ጣና ሐይቅን ለመታደግ 13 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጣና ሐይቅን መታደግ የተፈጥሮ ሚዛንን ጠብቆ የሕዳሴ ግድቡን የውኃ አቅም ዘላቂነት ማረጋገጥ መሆኑን በመገንዘብ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳድር የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች ከወር ደመወዛቸው እና ከተቋማቸው በማዋጣት 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ለጣና ሐይቅ እና አካባቢው ደኅንነት ፈንድ ገቢ እንዲሆን ወስነው ነበር፡፡
ቃላቸውን ወደ ተግባር በመቀየርም 13 ሚሊዮን ብር በክልሉ መንግስት የባንክ ሂሳብ ቁጥር ማስገባታቸውን ገቢዎች ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው በይፋዊ የመህበራዊ ተስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ጣና ሐይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ኀላፊዎችና ሠራተኞች ላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ አቶ ላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ጣናን መታደግ የሕዳሴ ግድቡን መታደግ በመሆኑ ከመቼም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ሚኒስትሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ