
የዘራፊውን፤ተስፋፊውንና የሀገር አፍራሹን ትህነግ ተልዕኮ በማክሸፍ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) በተደራጀ የሴቶች እንቅስቃሴ የሴቶችን ተሳታፊነትና እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ የአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ፌዴሬሽኑ 2ኛ ዙር 6ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በእንጅባራ ከተማ አካሂዷል፡፡
የአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ሴቶች ማህበር፤ የአማራ ነጋዴ ሴቶች ማህበር፤ የአማራ ደራሲያን ሴቶች ማህበርና የአማራ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ማህበርን በአባልነት በማቀፍ የክልሉን ሴቶች ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራ ነው፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ትልቅሰው ይታያል የአማራ ሴቶች በሕገ መንግስቱ የተሰጣቸውን የመደራጀት ነፃነት በመጠቀም ሴቶች በፆታቸው፤በሙያቸው፤በስራ ባህሪያቸውና በጉዳታቸው አይነት የየራሳቸውን ተልዕኮና ዓላማ አንግበው እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል፡፡ የክልሉን ሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ጥቅማቸው የተነካባቸው የጁንታው ቡድኖች በየአካባቢው ለመፍጠር ያቀዷቸውን የጥፋት ተልዕኮዎች በማክሸፍ ረገድም ሴቶች የላቀ ሚና እንደነበራቸው ወይዘሮ ትልቅሰው ገልፀዋል፡፡ ዘራፊው፤ተስፋፊውና ሀገር አፍራሹ የጁንታው ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሲፈጽም ሴቶች ለሕግ ማስከበሩ ስራ በግንባር ከመፋለም አንስቶ ስንቅ በማዘጋጀት፤ቁስለኛ በመንከባከብና ውሃ በማቀበል አኩሪ ገድል ፈፅመዋልም ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡
ፌዴሬሽኑ በቀጣይም የሴቶችን ዘላቂ የገቢ ማስገኛ ዘርፎችን በማስፋት የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሰደግና በአመራር ሚናቸው የውሳኔ ሰጪነትና ተደማጭነትን ለማሳደግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ተገልፃል፡፡
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ- ከእንጂባራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ