የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የትህነግን ጥፋት ዝረዝር ጉዳዮች ለሕዝብ እንደራሴዎች በማቅረብ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ማድረግ እንደሚገባው የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር የህግ አማካሪ አሳሰቡ፡፡

293

ባሕር ዳር፡ ህዳር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል መንግስት ዳተኝነት ለትህነግ አረመኔያዊ ተግባር ትልቁን ድርሻ የሚወሰድ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር የህግ አማካሪ መርኃጽድቅ መኮንን ተናግረዋል፡፡ አሁንም ቢሆን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዝረዝር የጥፋት ጉዳዮችን ለሕዝብ እንደራሴዎች በማቅረብ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ ሊሰራ እንደሚገባ ነው ያመላከቱት፡፡

ትህነግ እና ተላላኪው ኦነግ ሸኔ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል በአሸባሪነት የሚያስፈርጅ እና በጦር ወንጀለኛ ፍርድ ቤት የሚያስጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተቋማትን ማውደም እና ዘር ማጥፋት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሽብርተኝነት የሚያስፈርጅ የህግ ድንጋጌ መኖሩን አስረድተዋል፡፡

ዘራፊው የትህነግ ቡድን ገና ከጅምሩ አማራን እንደ ጠላት በመቁጠር የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል፤ የራሱን አስተሳሰብ በሃይል ሲጭን ነበር ነው ያሉት።

የህግ አማካሪው ለዚህም በአብነት ትህነግ በ1969 ዓ.ም ኢትዮጵያን ለመውረር ከመጣው ዚአድባሬ ወራሪ ሃይል ጎን የቆመ የሀገራችን ፀር ነው፤ በ1983 ዓ.ም ስልጣኑን ከተቆናጠጠ በኋላ በቀይ ባሕር ሃያለን ከነበሩ ሀገራት አንዷ የነበረችውን ኢትዮጵያ ወደብ አልባ አድረጎ እድገቷን ለቁልቁለት የዳረገ ከሃዲ ቡድን መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህም ሳይበቃ ኦነግ ሸኔ ትግራይ ክልልን ዋሻ አድርጎ እንዲጠቀም ፈቅዶለታል፤ ለጥፋ ተልእኮ በማሰማራት ዘግናኝ ወንጀሎችን እንዲሰራ አድርጎታል፤ የፋይናንስ እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ለዘመናት ያደረሰው ወንጀል በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ ህግ የሚያስጠይቅ እንደሆነ መርሀፅድቅ ጠቁመዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ደግሞ ድርጊቱ ለአሸባሪነት የሚያስፈርጅ መሆኑን በመገንዘብ ዝርዝር ጉዳዮችን ለፓርላማ (ለሕዝብ እንደራሴ) በማቅረብ ትህነግ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ መስራት አለበት ብለዋል። በሀገር መከላከያ ሠራዊት የፈጸመው ክህደት ደግሞ በጦር ወንጀለኛ ፍረድ ቤት የሚያስጠይቅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ትህነግ አሁን እየተወሰደበት ያለውን እርምጃ ትግራይን እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር በመቁጠር የአፍሪካ ኅብረት እና ደቡብ አፍሪካ እንደምታሸማግል መጠየቁም ለፌዴራል መንግስት ያለውን ንቀተ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል። የህግ አማካሪው የፌዴራል መንግስት አሁንም ጊዜ ሳይወስድ ጁንታውን ትህነግ በሽብርተኝነት በመፈረጅ ያለውን ሀብት መውረስ፣ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኝ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡-አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያልተረጋገጠ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አሳሰበ፡፡
Next articleወንበዴው እና ስግብግቡ የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።