ጎግል ኩባንያ ጎግል+ የተባለውን የማህበራዊ ትስስር ገጹን መዝጋቱን ገለጸ፡፡

371

ጎግል ኩባንያ ጎግል+ የተባለውን የማህበራዊ ትስስር ገጹን መዝጋቱን ገለጸ፡፡

በመረጃ ማፈላለጊያ አገልግሎቱ ታዋቂ የሆነው ጎግል ኩባንያ ውጤታማ እንዳልሆነ የተነገረለትን ጎግል + የተባለውን የማህበራዊ ትስስር አገልግሎቱን ከዛሬ ጀምሮ መዝጋቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ኩባንያው ይህን አገልግሎቱን በአውሮፓዊያኑ 2011 ይፋ ያደረገው ፌስ ቡክና ትዊተርን ከመሰሉ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር ለመዋዳደር እንደነበር ይነገራል፡፡

ለዚህም አገልግሎቱን በዩቱብ ተጠቃሚዎች በኩል ለማስፋፋት ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም የማህበራዊ ትስስር ገጹ ተወዳዳሪ መሆን እንዳልቻለ ነው የተገለጸው፡፡

በዚሁ አግልግሎት ላይ ከአውሮፓውያኑ 2011 መጨረሻ ጀምሮ የዘርፉ ተንተኛች ችግሮች እዳሉበት ሲገልጹ እንደነበርም ዘገባው አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጅ ኩባንያው የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጹን ለመዝጋት የወሰነው በ2018 በመረጃ ቀበኞች ጥቃት እንደ ደረሰበት ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ

Previous article540 ሚሊየን የፌስቡክ መረጃዎች በአማዞን ሰርቨር ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ
Next article ሳምሰንግ በዓለማችን የመጀመሪያ ነው የተባለለት በ5G ኔትዎርክ የሚሰራ ስማርት ስልክ በቀጣዩ ወር ለገበያ ሊያቀርብ ነው።