540 ሚሊየን የፌስቡክ መረጃዎች በአማዞን ሰርቨር ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ

147
A smartphone user shows the Facebook application on his phone in the central Bosnian town of Zenica, in this photo illustration, May 2, 2013. Facebook Inc's mobile advertising revenue growth gained momentum in the first three months of the year as the social network sold more ads to users on smartphones and tablets, partially offsetting higher spending which weighed on profits. REUTERS/Dado Ruvic (BOSNIA AND HERZEGOVINA - Tags: SOCIETY SCIENCE TECHNOLOGY BUSINESS) - RTXZ81J

 ከፌስቡክ የተሰበሰቡ 540 ሚሊየን መረጃዎች በኦንላይ ህዝብ የመረጃ ቋት ላይ እንደሚገኝ አፕጋርድ የተሰኘ የደህንነት ጥናት ተቋም አስታወቀ፡፡

እነዚህ መረጃዎች የሰዎች አስተያየቶችን፣ ላይኮችን፣ የተጠቃሚ ስሞችን እና የፌስቡክ መለያዎችን ያካተተ ነው የተባለ ሲሆን፥ ይህም በሁለት ሶስተኛ የፌስቡክ መተግበሪያዎች የተሰበሰበ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የፌስቡክ ፓሊሲ መረጃዎች በህዝብ የመረጃ ቋት እንዲሰበሰቡ የማይፈቅድ ሲሆን፥ አማዞን መረጃውን እንዲያነሳ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፌስቡክ ከአበልፃጊዎች ጋር በመሆን የደንበኞቻቸውን መረጃ ለመጠበቅ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ይህ በአማዞን ሰርቨር ላይ የተገኘው መረጃ ምንም አይነት ጥበቃ የማይደረግለት እንደነበረ ተነግሯል፡፡

የደህንነት ጥናት ተቋማት አማዞን የመረጃ ቋቱን ደህንነት እንዲያረጋግጥ ጥሪ ያቀረቡ ቢሆንም ኩባንያው ምንም አይነት እርምጃ እንዳልወሰደ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡-cnet

Previous articleአካል ጉዳተኞችን መመገብ የሚችል ሮቦት ይፋ ተደረገ
Next articleጎግል ኩባንያ ጎግል+ የተባለውን የማህበራዊ ትስስር ገጹን መዝጋቱን ገለጸ፡፡