አካል ጉዳተኞችን መመገብ የሚችል ሮቦት ይፋ ተደረገ

255

አዲስ አበባ፣መጋቢት 27፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ አካል ጉዳተኞችን መመገብ የሚችል ሮቦት መስራቱን ይፋ አድርጓል።

ሮቦቱ እንደ ሰው ልጆች መንቀሳቀስ የሚችል ሲሆን፥ አካል ጉዳተኞችን ምግብ ለመመገብ የሚያስችል ብቃት ያለው መሆኑም ተነግሯል።

ለዚህም ሮቦቱ ሳህን ላይ የተቀመጠን ምግብ ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት መሆኑ ነው የተገለፀው።

 

Embedded video

በተጨማሪም ምግቡን ለአካል ጉዳተኛው በትክክል ማጉረስ የሚያስችል የርቀት መለኪያ መሳሪያ የተገጠመለት መሆኑም በዘገባው ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም የተመጋቢውን የመጉረስ አቅም የመገመት አቅም አለው ነው የተባለው ሮቦቱ።

ሮቦቱ በርካታ አካል ጉዳተኞች ምግብ ለመመገብ የሚቸገሩበትን ሁኔታ ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን መሳሪያውን የሰሩት ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

Previous article‹‹ደስ ስላላችሁ ደስ ብሎኛል!›› አና ጎሜዝ-ለኢትዮጵያዊያን
Next article540 ሚሊየን የፌስቡክ መረጃዎች በአማዞን ሰርቨር ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ