ኪሊያን ምባፔ በ7 ተከታታይ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ፈረንሳዊ ተጫዋች ኾነ።

0
16

የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር ይህንን ታሪክ የሠራ የመጀመሪያው ፈረንሳዊ ተጫዋች ኾኗል።

ፈረንሳዊው ኮከብ በእነዚህ ሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረው በባየር ሙኒክ (በሁለት ጨዋታዎች)፣ በኢንተር ሚላን፣ በሮማ፣ በአርቢ ላይፕዚግ፣ በኤኢኬ አቴንስ እና በፒኤስቪ ላይ ነው።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ ከምባፔ በላይ በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር ቀዳሚ የኾኑት ሁለት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው፤ እነሱም በ11 ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረው ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና በ8 ተከታታይ ጨዋታዎች መረብ ላይ ያሳረፈው እንግሊዛዊው ሃሪ ኬን ናቸው።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_18_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here