በሊቨርፑል መለያ የግብ ቁጥሩን በእጥፍ ያሳደገው አሌክሳንደር አይሳክ!
የሊቨርፑሉ አጥቂ አሌክሳንደር አይሳክ ዘንድሮ በሁሉም ውድድር ግቦችን በማስቆጠር ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።
ስዊድናዊው አጥቂ በዚህም በዘንድሮው 2026/27 የውድድር ዘመን ለቀያዮቹ ያስቆጠራቸውን ግቦች 9 በማድረስ፤ በ2025/26 የውድድር ዘመን በ22 ጨዋታዎች አስቆጥሮት የነበረውን 4 ግብ በእጥፍ መብለጥ ችሏል።
አይሳክ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በ16 ጨዋታዎች 11 ግቦችን እና ለግብ የሚኾኑ ኳሶችን ማበርከት የቻለ ሲኾን፤ ይህም ባለፈው ዓመት በ22 ጨዋታዎች ካስመዘገበው 5 የግብ ተሳትፎ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሻሻል ያሳየበት ነው።
በተጨማሪም አሌክሳንደር አይሳክ ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር፤ እ.ኤ.አ ከ2021ዱ መሐመድ ሳላህ በኋላ ይህንን ታሪክ የሠራ የመጀመሪያው የሊቨርፑል ተጫዋች ኾኗል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_18_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



