ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ ትናንት ምሽት ሪያል ማድሪድ ፒ.ኤስ.ቪን 5 ለ 1 ባሸነፈበት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር አዲስ ታሪካዊ ክብረወሰን ጨብጧል።
በዚህም መሠረት ምባፔ በውድድሩ ታሪክ 75 ግቦች ላይ የደረሰ ሁለተኛው በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች መኾን የቻለ ሲኾን፣ ክብረወሰኑን የያዘው ሊዮኔል ሜሲ ብቻ ነው።
በተጨማሪም ተጫዋቹ በጥቂት ጨዋታዎች 75 ግቦች ላይ በመድረስ ከሊዮኔል ሜሲ እና ከሮበርት ሌዋንዶውስኪ ቀጥሎ ሦሥተኛው ፈጣን ተጫዋች ለመኾን በቅቷል።
ምባፔ በአጠቃላይ በሻምፒዮንስ ሊግ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በ6 ግቦች የኮከብ ግብ አግቢነቱን ከኮሞው ዶቪካስ ጋር በጋራ እየመራ ይገኛል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



