በቦልደር ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በመስበር ታላቁ ሩጫ አዲስ ክብረወሰን ሠበረ።

0
37

«ሩጫዬ ቀለሜ» በሚል መሪ መልዕክት የተካሄደው 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር፣ በዓለም የጎዳና ሩጫ ታሪክ አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ በታላቅ ድምቀት ተጠናቅቋል።

በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ ከ60 ሺህ በላይ ሯጮች የተሳተፉ ሲኾን፣ 50 ሺህ ተወዳዳሪዎች ውድድሩን በስኬት በማጠናቀቅ ሜዳልያ መውሰዳቸውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አረጋግጧል።

ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በአንድ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድር ላይ ውድድራቸውን ጨርሰው ሜዳልያ የወሰዱ ሯጮችን ብዛት ከፍ በማድረግ አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበ ኾኗል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ይሄንን ክብር የተጎናጸፈው የቦልደር የ10 ኪሎሜትር ሩጫ ውድድር ጨራሾችን በመብለጥ ነው።

ከዚህ ቀደም በአሜሪካ በሚካሄደው ታዋቂው የቦልደር 10 ኪሎ ሜትር (BolderBoulder 10K) ውድድር 47 ሺህ 645 ተወዳዳሪዎች ጨርሰው ሜዳልያ መውሰድ ችለዋል ።

በቦልደር ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በመስበር ነው ታላቁ ሩጫ አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበው።

#በሐናማርያም_መስፍን

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_13_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here