የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር 6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በሚካሄዱ ሦሥት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።
ከእነዚህም መካከል በተጠባቂው ጨዋታ 10 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ያስተናግዳል።
እስካሁን በዓመቱ ውድድር አንድም ጨዋታ ያላሸነፉት እና በሦሥት ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አፄዎቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ወደ ሜዳ ይገባሉ።
በ8 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ያምናው ሻምፒዮን ንግድ ባንክ በበኩሉ አሸንፎ ወደ መሪዎቹ ለመጠጋት ጠንካራ ፉክክር የሚያደርግበት ጨዋታ እንደሚኾን ይጠበቃል።
ሁለቱ ክለቦች እስካሁን በፕሪምየር ሊጉ ዘጠኝ ጊዜ ተገናኝተዋል። ንግድ ባንክ አምስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ የበላይነት ሲኖረው ፋሲል ከነማ 1 ብቻ አሸንፎ በቀሪ ሦሥት ጨዋታዎች አቻ መለያየታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ዛሬ በሚካሄዱ ሌሎች የፕሪምየር ሊጉ 6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀላባ፣ ነገሌ አርሲ ከጋሞ ጨንቻ ይገናኛሉ።
#በኃይሌ_አበራ
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_13_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



