በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ሊቨርፑል የምንጊዜም ተቀናቃኙን ማንቸስተር ዩናይትድን ዛሬ እሑድ ኅዳር 13/2019 ዓ.ም ምሽት 1:30 ላይ በአንፊልድ ስታዲየም ያስተናግዳል።
ጨዋታው በተለይ ለማንቸስተር ዩናይትድ አዲሱ አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ፈተና በመኾኑ ልዩ ትኩረት አግኝቷል።
በአሠልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ የሚመራው ሊቨርፑል ባደረጋቸው ያለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሦሥቱን በማሸነፍ እና በ18 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ወደ ጨዋታው ይገባል።
በአንጻሩ ያለፉትን አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የተሳነው ማንቸስተር ዩናይትድ በ8 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ከወራጅ ቀጣና ለመውጣት ይፋለማል።
በጨዋታው ቅድመ ግምት ሊቨርፑል በሜዳው የማሸነፍ ሰፊ ዕድል (56 ነጥብ 1በመቶ) ተሰጥቶታል።
ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጉት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ 3 ለ 2 ማሸነፉ ይታወሳል።
የዕለቱን ተጠባቂ ፍልሚያ ዳኛ ባሮት በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
በሌላ ጨዋታ ሀልሲቲ ብራይተንን ቀን 11፡00 ያስተናግዳል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_13_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



