ቤልጄማዊው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ቲቦ ኩርቱዋ በክለቡ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የሚያቆየውን አዲስ ውል በይፋ ፈርሟል።
ከመስከረም ወር ጀምሮ በቃል ደረጃ ተደርሶ የነበረው ስምምነት በዚህ ሳምንት በፊርማ መረጋገጡን የዝውውር መረጃዎች ጠቁመዋል።
በአዲሱ ስምምነት መሠረትም የ34 ዓመቱ ግብ ጠባቂ እስከ ሰኔ 2028 ድረስ በሳንቲያጎ በርናባው የሚቆይ ይኾናል።
ሪያል ማድሪድ የተጫዋቹን ውል መራዘም በመጪው ሳምንት በይፋ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



