አትሌቲኮ ማድሪድ የማንቸስተር ሲቲውን ኮከብ ለማስፈረም ወርቃማ ዕድል እየጠበቀ ነው።

0
58

በመጪው የጥር የዝውውር መስኮት የማንቸስተር ሲቲው ተጫዋች ማቴዮ ኮቫቺች በክለቡ ያለው የመሰለፍ ዕድል በመቀነሱ እና ባለው ሁኔታ ባለመርካቱ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተገልጿል።

የ32 ዓመቱ ክሮሺያዊው አማካይ በሲቲ ያለው ኮንትራት ወደ ማብቂያው እየተቃረበ በመኾኑ ክለቡ በጥር ወር በዝውውር ገንዘብ ለመሸጥ አለያም በክረምቱ በነፃ ዝውውር ሊያጣው የሚችልበት ዕድል እንዳለ ነው የተዘገበው።

በዚህ ወቅት የመጫወት ዕድል የሚፈልገው ኮቫቺች ወደ ስፔን ላሊጋ ሊመለስ የሚችልበት ዕድል እየታየ ሲኾን ቀደም ሲልም ፍላጎት ሲያሳይ የቆየው አትሌቲኮ ማድሪድ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል።

በተለይ አትሌቲኮ ማድሪድ የአማካይ መስመሩን ለማጠናከር እና ለቀጣይ የውድድር ዘመን ዕቅድ እየሠራ በመኾኑ የኮቫቺች ሁኔታ ለክለቡ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል ተብሏል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_11_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here