የ1 ሚሊዮን ዩሮ ሽልማትን ማን ይወስዳል?

0
48

ቫሌንሺያ ኅዳር 27/2019 ዓ.ም በሚካሄደው የቫሌንሺያ ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን (ሪከርድን) ለሚሰብር ማንኛውም አትሌት የ1 ሚሊዮን ዩሮ ሽልማት አዘጋጅታለች።

የወንዶች የዓለም ክብረ ወሰን 1:59:30 ሲኾን የሴቶች ደግሞ 2:09:56 ነው።

በተጨማሪም በወንዶች ከ2:04 በታች በመግባት ለሚያሸንፍ ወይም በሴቶች ከ2:19 በታች በመግባት ለሚያሸንፍ አትሌት የ80ሺህ ዩሮ ጉርሻ (ቦነስ) ተዘጋጅቷል።

479 ምርጥ (ኤሊት) ሯጮች ለውድድሩ የተመዘገቡ ሲኾን፣ ይህም በማራቶን ታሪክ ከተሠባሠቡት እጅግ ግዙፍ የምርጥ አትሌቶች ሥብሥብ አንዱ ያደርገዋል።
በወንዶች ዘርፍ የአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት የተሰጠው ኬንያዊው ጆን ኮሪር ነው።

ባለፈው ዓመት የቫሌንሺያን ውድድር በ2:02:24 ያሸነፈ ሲኾን፣ በሚያዝያ ወር በተካሄደው የቦስተን ማራቶን ደግሞ 2:01:52 በመግባት አሸንፏል።

የ44 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለም በተወዳዳሪዎች ዝርዝር ውስጥ የሚገኝ ሲኾን፣ የራሱን ክብረ ወሰ የኾነውን 2:04:15 ለማሻሻል ይሮጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በውድድሩ ከተካተቱት ሴቶች መካከል ፈጣኗ አትሌት ኢትዮጵያዊቷ ፎትየን ተስፋይ ስትኾን፣ በመጋቢት ወር በባርሴሎና ባደረገችው የመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯ 2:10:53 አስመዝግባለች።

የ10 ኪሎ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የኾነችው አግነስ ንጌቲች የመጀመሪያዋን የማራቶን ውድድር የምታደርግ ሲኾን፣ የአምናዋ አሸናፊ ጆይሲሊን ጄፕኮስጌይ ደግሞ የቦታውን ክብረ ወሰን በ2:14:00 ይዛለች።

ሁለት ታላላቅ አትሌቶች ግን በውድድሩ ላይ አይገኙም። የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ሳባስቲያን ሳዌ ራሱን ከውድድር ያገለለ ሲኾን፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ በልምምድ ወቅት ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከውድድሩ ወጥቷል።

የቫሌንሺያ ማራቶን የቦታውን ክብረ ወሰን (Course Record) ​በወንዶች ዘርፍ ኢትዮጵያዊው ሲሳይ ለማ (Sisay Lemma) እ.ኤ.አ በ2023 በተካሄደው ውድድር 2:01:48 በመግባት የቫሌንሺያ ማራቶንን ክብረ ወሰን ይዟል።​

በሴቶች ዘርፍ፦ ኬንያዊቷ ጆይሲሊን ጄፕኮስጌይ (Joyciline Jepkosgei) 2:14:00 በመግባት የሴቶችን የቦታው ክብረ ወሰን ይዛለች።

#ጥበቡ_ሰለሞን

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here